ዜናዎች

30-10-2025
የኮርፖሬሽኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የተከበሩ አቶ ኃይሌ አበበ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕድን ኃብት ልማት ቢሮ እና የኮርፖሬሽናችን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት እና ሁሉም የዋና ቢሮ አመራሮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነዉ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መብት አድማስ ኮርፖሬሽኑ…
30-10-2025
በኮርፓሬሽኑ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምገማ እና የ2018 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ማጠቃለያ ላይ መድረክ እንደ አካል ለስራ አመራር ቦርድ፣ ለኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፓሬሽን የዋንጫ ሽልማት አበርክቷል።

በሌላ በኩል ለተቋሙ ሁለንተናዊ ስኬት መረጋገጥ የጎላ ድርሻ ለነበራቸው ለኮርፖሬሽኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ለአቶ ኃይሌ አበበ እና ለኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መብት አድማስ እንዲሁም ለቀድሞው የስራ…
30-10-2025
ትልልቅ የመንገድ፣ ድልድይ እና ሌሎች መሰረተ-ልማት አውታሮችን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ኮርፖሬሽኑ አሰራሩን አውቶሜት በማድረግ ይበልጥ ለማዘመንና ውጤታማ ለመሆን የሚያስችለውን ERP ሶፍት ዌር እያስለማ ይገኛል፡፡ ከስራ ባህሪው አንጻር ከፍተኛ ሐብት የሚያንቀሳቅስ እና የሚጠቀም በመሆኑ እንዲሁም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ የተሳለጠ እና ዘመናዊ አሰራር እንዲሁም ሐብት አስተዳደር እንደሚያስፈልገው እሙን ነው። ይህንንም ተግባር…
30-10-2025
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ብቻ ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ በመስራት 256 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የኮርፖሬሽናችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መብት አድማስ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ገልጸዋል። እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ በያዝነው በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ እና በተግባር ምዕራፍ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን…
30-10-2025
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2030 ዓ.ም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከአፍሪካ ተመራጭ የግንባታ ተቋራጭ ለመኾን ራዕይ አስቀምጦ እየሠራ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ይህን ራዕዩን ለማሳካት ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጅ ተጠቅሞ መስራት አስፈላጊ መሆኑን የሚያምነው ኮርፖሬሽናችን በየጊዜው የተለያዩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በመግዛት አቅሙን ይበልጥ እያጠናከረ ይገኛል።

በያዝነው በጀት ዓመትም ኮርፖሬሽኑ የተለያዩ…