ከየት ወዴት| ራዕይ | ተልዕኮ | ዋና እሴቶች | አገልግሎቶች | ድርጅታዊ መዋቅር
ከየት ወዴት
ኅብር ኮንስትራክን ኮርፖሬሽን በዋናነት በመንገድ እና ድልድይ ግንባታ ዘርፍ የተሰማራ ደረጃ-1 ኮርፖሬሽን ነው። በመጀመሪያ በክልላችን ብሎም በሀገራችን እየተመዘገበ ካለው እድገትና ከህብረተሰቡ ፍላጎት ጋር እኩል የሚራመድ የመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታን ተደራሽ ለማድረግ ሲባል ከ397 ሚሊዮን ብር በማይበልጥ የመቋቋሚያ ካፒታል በደንብ ቁጥር 71/2002 ሲመሰረት የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በሚል ስያሜ በክልሉ መንግስት ተመሰረተ።
እስከ 2004 ዓ.ም በያኔው የአብክመ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ስር ሆኖ በባለስልጣኑ የሙያ፣ የሰው ሀይል እና የግብዓት ድጋፍ ሲደረግለት ከቆየ በኋላ በ2005 ዓ.ም የደረጃ አንድ ተቋራጭነት (GC-1) ፈቃድ አግኝቶ የራሱን ተቋማዊ አደረጃጀት ፈጥሮ መስራት ጀመረ። ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ የጠጠር መንገድ፣ የአስፓልት መንገድ፣ የህንጻ፣ የኮብል ስቶን፣ የካናል፣ የደረቅ ወደብ፣ የድልድይ እና ሌሎች የሲቪል ስራዎችን በጥራት ገንብቶ አገልግሎት እንዲሰጡ ሲያደርግ ቆይቷል፤ አሁንም እየገነባ ይገኛል።
በአነስተኛ ካፒታል የተቋቋመ ቢሆንም ከጊዜ ጊዜ ካፒታሉን እና የመፈጸም አቅሙን ይበልጥ እያሳደገ በመምጣቱ እና የያዛቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጨምሮ ወደ ፊት የሚይዛቸውን ሰፋፊ የልማት ስራዎች በብቃት ለማከናወን እንዲችል ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሚል በአዋጅ ቁጥር 214/2016 ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ አደገ። ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት ካፒታሉን 4 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ ሲሆን ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ፕሮጀክቶችን እየገነባ ይገኛል። የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ የማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ፕሮጀክቶች አሉት። በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ በ01 ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ በ03 ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፣ በ01 ኮርፖሬሽን ጽ/ቤት እና በ13 ዳይሬክቶሬቶች የተዋቀረ ነው።
ኮርፖሬሽናችን ለመንገድ እና ድልድይ ግንባታ የሚያስፈልጉ ሁሉንም አይነት የስራ መሳሪያዎች እና ማሽነሪዎች በበቂ መጠንና ጥራት ያሟላ ሲሆን በሰው ሀይል ረገድም በአብዛኛው በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ እንዲሁም አስፈላጊውን እውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ ያካበቱ ከ800 በላይ ባለሙያዎች አሉት፡፡ በየአመቱ በሚያከናውናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ለብዙ ሽህ ዜጎች የተለያዩ ጊዜያዊ የስራ እድሎችን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ለበርካታ ማሽንና ተሽከርካሪ አከራዮች፣ ግብዓት አቅራቢዎች፣ በማህበር ለተደራጁ ንኡስ ተቋራጮች የስራ ዕድሎችን በመፍጠር የራሳቸውን ካፒታል እንዲያፈሩ እንዲሁም የእውቀትና ክህሎት ሽግግር ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በክልላችን እና ከክልላችን ውጭ የግሉ ዘርፍ ደፍሮ ሊገባባቸው በማይችልባቸው አስቸጋሪ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ባላቸው እንዲሁም መሰረታዊ ግብዓቶች ባልተሟሉባቸው በየትኛውም አካባቢዎች ሁሉ በይቻላል መንፈስ በመግባት ጥራቱን የጠበቀ መንገድ ሰርቶ እያስረከበ ይገኛል፡፡ ለግንባታ ጥራት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ በመሆኑ ጥራት የኮርፖሬሽናችን መለያ እና የስራ ባህል ሆኗል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ የጊዜን ፋይዳ በውል ተገንዝቦ ተጨማሪ ሰዓታትን በመስራት ፕሮጀክቶችን ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድሞ የማጠናቀቅ በጎ ጅምር እያዳበረ ይገኛል። በዚህም ህዝባዊ ወገንተኝነትን የተላበሰ ተቋም መሆኑን አረጋግጧል። በአሁኑ ሰዓት ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚገነባቸው የተለያዩ ግንባታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በአስፓልት መንገድ እና ድልድይ ግንባታ ስፔሻላይዝ በማድረግ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመገንባት ኃላፊነት ወስዶ በጥራት በማከናወን ላይ ነው።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!
ራዕይ
በአፍሪካ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በ2030 ተመራጭ ሆኖ ማየት፤
ተልዕኮ
መሰረተ ልማቶችን በጥራትና በፍጥነት በመገንባት ትርፋማ ተቋም መፍጠር፤
- የቡድን ስራ
- ወጪ ቆጣቢነት
- ትጋት
- ግልጽነት
- ታማኝነት
አገልግሎቶች
- መንገዶችንና ድልድዮችን መገንባት፣ ደረጃ ማሻሻልና መጠገን፤
- ሌሎች የሲቪል ሥራዎችን ማከናወን፤
- የኮንስትራክሽን ገበያውን ማረጋጋት፤
- የግንባታ መሣሪያዎችንና ቁሣቁሶችን ማምረት፣ ማስመጣት፣ ማከራየትና መሸጥ፤
- በልማቱ ውስጥ ብቁ ተዋናይና ውጤታማ መሆን፤
- የአሰራር እና የውጤት ሞዴል መሆን እና፤
- በኢንቨስትመንትና በአክሲዮን ገበያው መሣተፍ፤
ድርጅታዊ መዋቅር
