News

23-11-2026
በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ኮርፖሬሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት ለመፈጸም ያቀደው የፊዚካል፣ ፋይናንሻል፣ የግብዓት አቅርቦት ዕቅድ ቀርቦ በመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ከፊዚካል ዕቅድ አንጻር በ2019 በጀት ዓመት ከ90 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት እና ውል የገባባቸውን ድልድዮች ግንባታ 65 % ለመፈጸም መታቀዱን የፕላንና ቢዝነስ…
23-11-2026
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አመርቂ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር መብት አድማስ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደገለፁት ከፊዚካል ዕቅድ አንጻር ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት በዌትድ አቨሬጅ የዕቅዱን 75.59 % መፈጸም ችሏል።
ከፋይናንሻል ዕቅድ አንጻር ደግሞ 5.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት 800 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ የዕቅዱን 82.13 % በመፈፀም 700…
23-11-2026
ኮርፖሬሽኑ ለወራቤ ቦዥባር አስፋልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ዘመናዊ እና ትልቅ የማምረት አቅም ያለው አዲስ አስፋልት ፕላንት ግዥ በመፈጸም ለስራ ዝግጁ ማድረጉን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ እንዳለው ደጉ ገልጸዋል። የወራቤ ቦዥባር አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት የአካባቢው ማህበረሰብ በጉጉት የሚጠብቀው ፕሮጀክት እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው ፕሮጀክት ነው ያሉት ኃላፊው ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዓመታት ይጠቀምበት የነበረው የኪራይ አስፋልት ማቅለጫ ማሽን ስራው የሚፈልገውን…
23-11-2026
ኮርፖሬሽኑ በክልሉ መንግስት ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 214/2016 ዓ.ም መሰረት ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ ሲያድግ የንግድ ምልክት ወይም ሎጎ ለውጥ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ኮርፖሬሽኑ የንግድ ምልክቱን በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በማስመዝገብ ባለቤትነቱን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ በብቸኝነት ለመጠቀም የሚያስችለውን የባለቤትነት መብት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማግኘት ችሏል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን…
30-10-2025
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የአደረጃጀት፣ የስያሜ እና የሎጎ ለውጥ ይፋዊ የማስተዋወቂያ እና የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የኮርፖሬሽኑ መሪዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኃይሌ አበበ የቀድሞው የአማራ…