ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት አመርቂ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉ ተገለፀ።

HCC
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት አመርቂ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር መብት አድማስ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደገለፁት ከፊዚካል ዕቅድ አንጻር ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት በዌትድ አቨሬጅ የዕቅዱን 75.59 % መፈጸም ችሏል።
ከፋይናንሻል ዕቅድ አንጻር ደግሞ 5.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት 800 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ የዕቅዱን 82.13 % በመፈፀም 700 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል።
በተያያዘም ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት ካሳካቸው ስኬቶች አንዱ በቴክኖሎጂ ታግዞ መስራት መቻል መሆኑን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ለአብነትም የተቀናጀ የሀብት አጠቃቀም (ERP)፣ CCTV Camera፣ GPS እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ ቋሚ ኃብት ከማፍራት አንጻር ከ 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኮንስትራክሽን ስራ ወሳኝ የሆኑ ሰባት ማሽነሪዎችን ግዥ በመፈጸም አቅሙን ለማጠናከር ጥረት ተደርጓል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን !
ለተጨማሪ መረጃዎች የኮርፖሬሽኑን የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ:-
Facebook: https://facebook.com/HibirConstructionCorporation
Youtube: https://www.youtube.com/@HibirConstructionCorporation
Telegram: https://t.me/hibirconstructioncorporation
Website: https://hibircon.et