ኮርፖሬሽኑ በ2019 በጀት ዓመት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማመንጨት 1 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ለማግኘት አቅዷል።

ኅብኮን ፕላን ዳይሬክቶሬት
በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ኮርፖሬሽኑ በተያዘው በጀት ዓመት ለመፈጸም ያቀደው የፊዚካል፣ ፋይናንሻል፣ የግብዓት አቅርቦት ዕቅድ ቀርቦ በመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ከፊዚካል ዕቅድ አንጻር በ2019 በጀት ዓመት ከ90 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት እና ውል የገባባቸውን ድልድዮች ግንባታ 65 % ለመፈጸም መታቀዱን የፕላንና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተገኘ ወርቁ ገልጸዋል።
አቶ ተገኘ እንደገለጹት ከፋይናንሻል ዕቅድ አኳያ ከ 10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማመንጨት 1 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ለማስመዝገብ ታቅዷል።
በተያያዘም የበጀት ዓመቱን የፊዚካል እና ፋይናንሻል ዕቅድ ለመፈጸም አስፈላጊ ማሽነሪዎችንና ግብዓቶችን በወቅቱ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ ተገኘ ወርቁ አስታውቀዋል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን !
ለተጨማሪ መረጃዎች የኮርፖሬሽኑን የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ:-
Facebook: https://facebook.com/HibirConstructionCorporation
Youtube: https://www.youtube.com/@HibirConstructionCorporation
Telegram: https://t.me/hibirconstructioncorporation
Website: https://hibircon.et